EmnetBridge

Your church, in your hand

ቤተ ክርስቲያንዎ በእጅዎ።

ደብርዎ ዜናውንና የአገልግሎት ሰዓቱን የሚያሳውቅበት፣ ጸሎቱና የዕለቱ ምንባብ በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር የሚጠብቅዎት፣ አሥራትዎም ያለ መካከለኛ በቀጥታ ቤተ ክርስቲያን የሚደርስበት መተግበሪያ፤ እምነት።

ዛሬ መስከረም ፳፭ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም.

Meskerem 25, 2019

የእምነት የቀን መቁጠሪያ፣ መስከረም ፳፻፲፱ ዓ.ም.፣ በግእዝ ቁጥሮችና በዕለቱ በዓላት
ከመተግበሪያው፦ የመስከረም የቀን መቁጠሪያ

መተግበሪያው

ምእመኑ የሚያገኘው

ነፃ፤ በአማርኛ፣ በትግርኛ፣ በአፋን ኦሮሞና በእንግሊዝኛ።

ደብርዎን ያግኙ፤ ሕይወት የትም ብትወስድዎ

በስም ወይም በከተማ ይፈልጉ፤ ወይም ካርታውን ከፍተው በአቅራቢያዎ ያሉትን አጥቢያዎች ይመልከቱ። የራስዎን ደብር ይከተሉ፤ ክርስትና የተነሡባትንም።

አብያተ ክርስቲያናትን ማግኛ፦ በባልቲሞርና በዋሽንግተን አካባቢ ያሉ የኦርቶዶክስ አጥቢያዎች ካርታና ዝርዝር

ዜናውን ከደብሩ ራሱ ይስሙ

ማስታወቂያ፣ ስብከት፣ መርሐ ግብርና የአገልግሎት ሰዓት በቀጥታ ከደብሩ ጽሕፈት ቤት ይደርስዎታል፤ ለአራተኛ ጊዜ የተላለፈ የማስታወቂያ ፎቶ ሆኖ አይደለም።

በእምነት ውስጥ የአንድ ደብር ገጽ፦ አድራሻ፣ ካርታ፣ ልጥፎች፣ መርሐ ግብሮች፣ ዘመቻዎችና አገልግሎቶች

የጸሎት ሰዓታትን ይጠብቁ

ውዳሴ ማርያም፣ መዝሙረ ዳዊት፣ የዕለት ጸሎትና የዕለቱ ምንባብ። በመተግበሪያው ውስጥ ስለሚገኙ ኢንተርኔት በሌለበትም ይከፈታሉ።

የጸሎት መጻሕፍት በእምነት፦ የዕለቱ ምንባብ፣ ውዳሴ ማርያም፣ መዝሙረ ዳዊትና ሌሎችም

ሦስት እርምጃዎች

  1. መተግበሪያውን ያውርዱ በ iOS እና በ Android ነፃ።
  2. ቤተ ክርስቲያንዎን ያግኙ ይፈልጉ፣ ወይም ካርታውን ይመልከቱ።
  3. «ይከተሉ» የሚለውን ይጫኑ ከዚያ በኋላ ዜናዋ ወደ እርስዎ ይመጣል።
በቅርቡ App Store በቅርቡ Google Play

በቅርቡ በ App Store እና በ Google Play

ለካህኑ፣ ለሰበካ ጉባኤውና ለገንዘብ ያዡ

አንድ ጊዜ ይለጥፉ፤ ሁሉም ስልክ ይድረስ።

የደብሩ ጽሕፈት ቤት እምነትን በስልክ ወይም በድር ፖርታሉ ያስተዳድራል። የኮምፒውተር ባለሙያ መሆን አያስፈልግም።

ዜናና መርሐ ግብር
ማስታወቂያውን ቅዳሜ ማታ ይጻፉ፤ እሑድ ከቅዳሴ በፊት በሁሉም ምእመን ስልክ ላይ ይገኛል።
ሒሳብ የሚቀርብበት ስጦታ
ፈንዶች፣ ዘመቻዎች፣ የስጦታ ቃሎች፣ ተመላሽና ወጪ ክፍያዎች፤ ሰበካ ጉባኤው የሚያነበው፣ ገንዘብ ያዡም የሚያወርደው ሪፖርት።
ምእመናንዎ በአንድ ዝርዝር
ደብርዎ በትክክል የሚጠቀምባቸው መስኮች ያሉት የአባላት መዝገብ፣ በ CSV ማስገባትና የአባልነት ክፍያ ክትትል።
ለእያንዳንዱ የሚገባው ቁልፍ
ገንዘብ ያዡ ገንዘቡን፣ የሚዲያ ቡድኑ ልጥፎቹን፣ ሰንበት ትምህርት ቤቱም የራሱን ቡድን ያያል።

እያንዳንዱን የደብር መለያ እኛው እንከፍታለን፤ ጽሕፈት ቤቱንም እናለማምዳለን። ራስን መመዝገብ የለም።

የእምነት የደብር አስተዳደር መነሻ፦ ልጥፎች፣ መርሐ ግብሮች፣ የቀን መቁጠሪያ፣ ስጦታ፣ ምእመናንና ሌሎችምየደብሩ ልጥፎች፦ ስብከቶችና የመዝሙር አገናኞች ከእይታ ብዛታቸው ጋርየዚህ ወር ስጦታ፦ ከአምስት ሰዎች $700፣ ከክፍያዎች፣ ፈንዶች፣ ዘመቻዎችና ወጪ ክፍያዎች ጋር

ስጦታ

ስጦታዎ ወዴት ይሄዳል

ወደ ደብሩ። እያንዳንዷ ቤተ ክርስቲያን የራሷ የ Stripe ሒሳብ አላት፤ ስጦታውም እዚያ ይገባል። እምነት የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ በእጁ አያቆይም።

በመረጡት መንገድ ይስጡ

አንድ ጊዜ፣ በየሳምንቱ ወይም በየወሩ፤ ቤተ ክርስቲያንዎ ወደከፈተችው ፈንድ፦ ለሕንጻ፣ ለወጣቶች፣ ለነዳያን። የስጦታ ቃል ገብተው ዓመቱን ሙሉ ይከታተሉ።

የሠራውን ይመልከቱ

ዘመቻዎች ሂደታቸውን ያሳውቃሉ። ይከታተሉ፣ አስተያየት ይስጡ፣ በ«አሜን» ይመልሱ።

አንድ ስጦታ፣ በግልጽ

የሚሄደው
ወደ ደብርዎ የራሱ ሒሳብ
የእምነት ድርሻ
የ3% የመድረክ ክፍያ
የካርድ ማስኬጃ
የ Stripe መደበኛ ተመን
ለቤተ ክርስቲያን ወርሃዊ ክፍያ
የለም
ደረሰኝ
ለእያንዳንዱ ስጦታ፣ በኢሜይል
የዓመት መጨረሻ መግለጫ (አሜሪካ)
ለግብር ዝግጁ

ክፍያዎች በ Stripe ይስተናገዳሉ። ለኢትዮጵያ የአገር ውስጥ የክፍያ አማራጮች በዕቅዳችን ውስጥ ናቸው።

እምነት

እምነት ሃይማኖት ነው፤ መተማመንም ነው።

ሁለቱንም ለመጠበቅ እንተጋለን። ስጦታዎ ከቤተ ክርስቲያንዎ በቀር ወደ ሌላ አይሄድም። የደብርዎ መዛግብት የደብርዎ ናቸው። ጸሎቶቹ የቤተ ክርስቲያን የራሷ ቃላት ናቸው እንጂ የእኛ አይደሉም።

ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን፣ በዓለም ዙሪያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዓለም ካሉ ጥንታዊ የክርስትና ትውፊቶች አንዷ ናት። «ተዋሕዶ» በግእዝ «አንድ መሆን» ማለት ነው። ዛሬ ምእመናኗ ከአዲስ አበባ እስከ ዋሽንግተን፣ ለንደንና ሲድኒ ባሉ አጥቢያዎች ይሰበሰባሉ።

የሚጠየቁን ጥያቄዎች

እምነት ነጻ ነው?

አዎ። መተግበሪያው ለምእመናን ነጻ ነው። አብያተ ክርስቲያናት ወርሃዊም ሆነ የማስጀመሪያ ክፍያ አይከፍሉም፤ በእያንዳንዱ ስጦታ ላይ ያለ ትንሽ የመድረክ ክፍያ (በነባሪ 3%) እና መደበኛ የካርድ ማስኬጃ መድረኩን ያስቀጥላሉ።

ስጦታዬ በትክክል ወዴት ይሄዳል?

በቀጥታ ወደ ቤተ ክርስቲያንዎ። እያንዳንዷ ቤተ ክርስቲያን የራሷን የ Stripe ነጋዴ ሒሳብ ትከፍታለች፤ ስጦታዎም እዚያው ይቀመጣል። እምነት የቤተ ክርስቲያንዎን ገንዘብ አያቆይም።

እምነት በየትኞቹ ቋንቋዎች ይናገራል?

English፣ አማርኛ፣ ትግርኛ እና Afaan Oromoo። ቀናትም በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በግእዝ ቁጥሮች ሊታዩ ይችላሉ።

እምነት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ብቻ ነው?

አዎ። እምነት የተሠራው ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አጥቢያዎችና ለምእመኖቻቸው ነው፦ የኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር፣ በዓላትና አጽዋማት፣ ጸሎቶች እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኒቱ ቋንቋዎች።

ቤተ ክርስቲያኔ እንዴት ትቀላቀላለች?

በ support@emnetbridge.com ይጻፉልን። የእምነት ቡድን እያንዳንዱን የቤተ ክርስቲያን መለያ አረጋግጦ ይከፍታል፤ ከዚያም የደብርዎን ጽሕፈት ቤት በፖርታሉና በክፍያ ምዝገባው ያስተዋውቃል።

መረጃዬ አስተማማኝ ነው?

መረጃ በመተላለፊያ ወቅት ይመሰጠራል፣ የየቤተ ክርስቲያኑ መዛግብት በተናጠል ይጠበቃሉ፣ መረጃዎን መውሰድም ሆነ መለያዎን መሰረዝ በመተግበሪያው ውስጥ በማንኛውም ጊዜ ይቻላል።

መተግበሪያዎቹ መቼ ይለቀቃሉ?

የ iOS እና የ Android መተግበሪያዎች በመጨረሻ ዝግጅት ላይ ናቸው። መደብሮቹ እንዳጸደቁ በዚህ ገጽ ያሉት አገናኞች ወዲያውኑ ሥራ ይጀምራሉ።

ለካህኑ፣ ለሰበካ ጉባኤውና ለገንዘብ ያዡ

እምነትን ለደብርዎ ከፈለጉ፣ የደብሩን ስምና ከተማ፣ ገንዘቡንም ማን እንደሚያስተዳድር ጽፈው ይላኩልን። መለያውን እንከፍታለን፣ ጽሕፈት ቤቱን በፖርታሉ እናለማምዳለን፣ ስጦታውንም ከደብሩ የራሱ የባንክ ሒሳብ ጋር እናገናኛለን። ወርሃዊም ሆነ የማስጀመሪያ ክፍያ የለም።

የእምነት ብሪጅ ቡድን